ሰውን ማዕከል ያላደረገ የብልፅግና ጉዞም አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ መሆኑን በቅጡ እንረዳለን፡፡
ለዚያም ነው ወደህዝባችን ወርደን በቅርበት ለማገልገል ሌት ተቀን እንትጋ እያልን በየደረጃው ላሉ አመራሮቻችን የህዝብ አደራ አሰጨብጠን መላካችን፡፡ በእኔ አውቅልሀለሁ የአመራር ዘይቤ እንኳን ሀገር ቤተሰብ አይመራም፡፡
ህዝባችንን በየጊዜው ማማከር፣ ማወያየትና በተግባር ማሳተፍ በመቻላችን እንወጣው ይሆን ብለን ቆም ብለን ያሰብንባቸውን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካትና ውጤታቸውን ማጣጣም ችለናል፡፡”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ