በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ አቶ መለሰ ዓለሙ እንደተናገሩት በ60 ቀናት ከሚተገበሩ ሰው ተኮር ተግባራት መካከል አንዱ ከተማውን በማስዋብ እንደ ስሟ አዲስ በማድረግ የህብረተሠባችንን የአኗኗር ሁኔታ በመቀየር ረገድ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው። በመሆኑ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በሙሉ አካባቢውን የማስዋብ ስራ በስፋት በመሳተፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለእነዚህ ተግባራት ስኬት ነዋሪዎች ባለሀብቶችና አመራሮች በተቀናጀ መልኩ በመስራት ከግብ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አቶ መለሰ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ በበኩላቸው ሰዎች በንፁህና አረንጓዴ ስፍራ የመኖርና ንፁህ አየርና ለጤና ተስማሚ የሆነ ስፍራን የማግኘት መብት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለፁት የነዋሪዎቹን ፍላጎት ለማሟላት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት መላው የክፍለ ከተማችንን ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶችና በጎ ፍቃደኞች ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።