የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና በተዋረድ ባሉ መዋቅሮች የ2015 በጀት አመት የስድስት ወራት የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ላይ ትኩረት በማድረግ በተከናወነው ሱፐርቪዥን ላይ የሱፐርቪዥኑን ግኝት ሪፖርት ለከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቅረብ ውይይት ተካሒዷል።
በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የፓለቲካና የድርጅት ስራዎችን ሱፐርቪዥን ላከናወኑ የቡድኑ አባላት ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተከናወነው ሱፐርቪዥን አቅም የሚሆን እና በቀጣይም ለምንሰራው ስራ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የህዝብና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የሱፐርቪዥኑን ዓላማ አስመልክቶ እንደገለጹት የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት የስድስት ወር የፓለቲካና የድርጅት ተግባራት አፈጻጸም በመዳሰስ የታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት ለማረም እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ ለማስፋት እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አዲሱ አክለውም በከተማዋ ያሉ ሶስት ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ ከእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ሁለት ወረዳዎችን በመለየት ሀቀኝነትና ሚዛናዊነት በተሞላበት መልኩ እንዲሁም ጥንካሬና ድክመትን ሊያሳይ በሚችል ሁኔታ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን መከናወኑን ተናግረዋል።