ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ 1503 ወጣቶች፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጓል።
በበድጋፍ ርክክብ እና የዘማች ሽኝት መርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን፣ሉዐላዊነቷ እና አንድነትቷ እንዲጠበቅ ልጆቷ በቆራጥነት ይሰራሉ ብለዋል ።
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በእብሪት እና በድፍረት ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በቁም ቅዠት ውስጥ ገብቷል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህ ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠታቸው መቼም ቢሆን አይሳከላቸውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ በጉልበት የመጡባትን አካላት ታሸንፋቸዋለች ለዚህ ደግሞ ታሪክ ምስክር መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ አሁንም አሸባሪው ሀይል በአማራና አፋር ድባቅ እየተመታ ነው ብለዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አለምጸሃይ ሽፈራው በበኩላቸው የ የአይነት ድጋፉ 142 ሰንጋዎች፣ 167 በጎችና የተለያዩ የምግብ እና የመድኃኒት ግብአቶችን ጨምሮ ለህልውና ዘመቻው ያሰባሰበውን 90 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ መሰባሰቡን ገልጸዋል ።
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊቱን ከመደገፍ ባለፈ የአካባቢውያቸውን ሰላም እና ጸጥታ ለማስጠበቅ ባለፉት ቀናት ከ24ሺህ በላይ ህዝባዊ ሰራዊት ስልጠና መሰጠቱን ወ/ሮ አለምጸሀይ ገልፀዋል፡፡
በሽኝት መርሐግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ፣ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴው ግድብ ዋና ተደራዳሪና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ኢ/ር ስለሽ በቀለ፣ አርበኞች እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የክ/ከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
-አካባቢህን ጠብቅ
_ ወደ ግንባር ዝመት
_ መከላከያን ደግፍ