አባገዳዎች የከተማ አስተዳደሩ በችግራችን ወቅት ከጎናችን በመቆም ያደረገው ድጋፍ ለተጎጂዎቹ መድረሱን ገልፀው ለዚህም ምክር ቤቱ የከተማውን አመራር እና መላውን የአዲስ አበባ ነዋሪ አመስግነዋል::
የዞኑን ህዝብ በመወከል የመጡት አባገዳዎች ለም/ቤት እና የካቢኔ አባላት የቦረናን ህዝብ የባህል አልባሳት በስጦታ አበርክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ድርቅ ተጐጆዎች ከ252 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።