የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያሰባሰቡትን ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ፣ እየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን ፣በልሲቲ ነገሳ ትሬዲንግ የግል ድርጅት ፣ባለዛፍ የአልኮልና መጠጥ ድርጅትና ፊቨን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ናቸው።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ አገራችን ሁላችንም ተባብረን የምንገነባት በመተሳሰብ አብረን የምንኖርባት መሆን ሲገባ በተፈጠረው ጦርነት በየአካባቢው ከመደበኛ ህይወት ውጪ የሚኖሩ ወገኖቻችን ቁጥራቸው ከፍተኛ ሆኗል ብለዋል።
ለዚህም ኢትዮጵያዊነትን ተላብሰን ትምህርትና ጤና ላጡ ህፃናት ፣ እናቶችና አዛውንቶች በተመሳሳይ የዕለት ፍጃታ ላጡ ወገኞቻችን በጋራ ልንደርስላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
በጦርነቱ የወደሙ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መንግስት መልሶ ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ህዝቦች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ምክትል ከንቲባዉ ጠይቀዋል፡፡