በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ተፎካካሪ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮዎች በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ።

ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፣መኢአድ ፣የህዳሴ ፓርቲ፣የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ፣የአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና የሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የህዝብ ላይብረሪ እና የአድዋ ዐዐ ኪሎሜትር የፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።