በዛሬው እለት በቂርቆስ ክ/ከተማ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማእከል ተጠቃሚ የነበሩ ሴቶች በልብስ ስፌት ሰልጥነው ተመርቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
የተስፋ ብርሃን ምገባ ማእከል ከተቋቋመ አንድ አመት የሆነው ሲሆን የዛሬ አመት ማዕከሉ ሲከፈት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር እንመግባለን ስንል ስንፍናን እንዳያበረታታ ፤ ከመመገብ ባሻገር የስልጠና እና የስራ እድል መፍጠርያ እንዲሆን በትኩረት የምንሰራበት ይሆናል ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡
ቃል በተግባር እንዲሉ እነሆ ዛሬ በምገባ ማእከሉ ተጠቃሚ የነበሩ እና በመጋቢነት ሲያገለግሉ የነበሩ እናቶች ሰልጥነው ወደሚቀጥለው የህይወት ምእራፍ በመሸጋገራቸው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የተስፋ ብርሃን ምገባ ማእከላት እንደዚህ አይነት ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ሌሎችም ተባባሪ ወገኖች በእንደዚህ አይነት ተግባር በመሳተፍ ለወገኖቻችሁ የተስፋ ብርሃን ሁኑ ለወገኖቻችሁ አቅም ሁኑ፤ ስልጠና በመስጠት ፤የስራ እድል በመፍጠርና በተለያየ መንገድ ተሳተፉ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለአንድ አመት ያህል በተቋሙ ላይ የምግብ ወጪውን በመሸፈን ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ የቆየው ሮሃ ሄልዝ ፋውንዴሽን ለክብር ህይወት ቤተክርስቲያን ርክክብ ፈፅሟል፡፡