ብዙዎቻችን የምናውቀው ወጣት ኤፍሬም በለጠ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ሲመረቅ በርካቶች ያልደፈሩትን የእናቶች ሸክም በአደባባይ የመሰከረ ለእናቶችም የሚገባውን ክብር ያሳየ ደግነታቸውንና የሚያልፉበትን የህይወት ውጣ ውረድ በአደባባይ በመመስከር ለበርካቶች አርአያ መሆኑን ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ በሌላ አዲስ ምዕራፍ ህዳርን ተከትሎ ከህዳር ሲታጠን ወደ ኢትዮጵያን እናጥን” ያሻግረናል ።
ወጣት ኤፍሬም በለጠ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን እናጥን በሚል መሪ ቃል በከተማችን በየወረዳው ያሉ የህዝብ መገልገያ የሆኑ ኮምፒውተሮችን እየዞረ እያፀዳና በብልሽት የተቀመጡትን እየጠገነ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በማድረግ ኢትዮጵያን ንብረቷ እንዲያገለግላት እየጠገነ ነዉ።
ቀጣይም ኢትዮጵያን ከሌቦችና ከሙሰኞች ሊያፀዱ የሚችሉ ዲጂታል መተግበርያዎችን በማበልፀግና በመተግበር ተቋማት ግልጽና ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጡና መንግስት ዜጎች የሚፈልጉት አገልግሎት ከሙስና በፀዳ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ከሚያደርገው ትግል ጎን በመቆም ኢትዮጵያ ካጎነበሰችበት ቀና እንድትል የማይቋረጥ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል ።
“እንስራ ሀገራችንን እናበልፅግ!!
”ኢትዮጵያን ከሙስና እናፅዳ!!