ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገር ላይ የተከፈተውን የተዛባ ትርክት ወደ ኋላ በመግፋትና በመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና እንዲጫዎት ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሩቅ እና ቅርብ ያሉ የአገራችንን በጎ የማይፈልጉ አካላት ያለ የሌለ ሀብትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው በአገራችን ላይ የተበላሸ ትርክትን የመጫን ጦርነት ውስጥ መክፈታቸውን አንዘንጋ ብለዋል።
በብሔር ላይ እየተሠራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት አለበትም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በሕብረ ብሔራዊ አንድነት የራሳችንን ታሪክ እኛው እንሠራለን እኛው እንጽፋለንም ብለዋል በመልዕክታቸው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!