በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገዥና ተቃዋሚ የሚለው የፖለቲካ ትርክት እየተቀየረ በአንድ በኩል በሀሳብ ፉክክር በሌላ በኩል ደግሞ በሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች የመተባበር ባህል መጎልበቱን አስረድተዋል።
መርሃ ግብሩ አረንጓዴ አሻራን ከማሳረፍ በተጨማሪ ለዴሞክራሲ ግንባታም አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት ኃላፊው በቀጣይም የትኛውም ፓርቲ ያሸንፍ በአገራዊ ጉዳዮች በጋራ እንደምንቆም ያሳየንበት ነው ብለዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባቴ የመሪዎች ራዕይ ወደ ህዝብ ወርዶ ፍሬያማ የሚሆነው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በአገራዊ ጉዳዮች በጋራ ሲቆሙ ነው ብለዋል። ያሸነፈም የተሸነፈም እኩል ኢትዮጵያዊ
ስለሆነ ልማት ላይ በጋራ እንሰራለን ያሉት ዶክተር ራሄል ቀጣዩን ትውልድ ለመገንባት ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም በማየት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን አመስግነዋል።
የየክ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በክረምት የተከልናቸውን ችግኞች በበጋው ወቅትም አብረን እንከባከባቸው የሚል ጥሪ አቅርበውላቸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው እስካሁን በከተማው 5ሚሊዮን ገደማ ችግኝ የተከለ ሲሆን በነገው ዕለትም በአንድ ጀምበር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል ። በዚህም መርሃ ግብር ሁሉም የከተማው ህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ እንዲሆን መልዕክት ተላልፏል ።
በዛሬው ዕለት በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙን ጨምሮ በሚኒስትር ማዕረግ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባቴ እና የክ/ከተማው አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋ