– 119 ኘሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል
– የታላላቅ ነባር ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀም በተመለከተ
አድዋ ሙዚየም ግንባታ 78 %
የትራንስፖርት ክላስተር ግንባታ 52.12%
የአመራር አካዳሚ ግንባታ 56%
የካ መኪና ማቆሚያ /ሾላ ፓርኪንግ/ ግንባታ 74.7% ማድረስ ተችሏል፡፡
– ዘላቂ የስራ እድል ለመፍጠር የተጀመረው በከተማችን የመጀመሪያ የሆነው የቂሊንጦ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ክላስተር ግንባታ በፍጥነት እና በጥራት እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ ለበርካታ የከተማችን ወጣቶች ዘላቂ የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል:: በአሁኑ ወቅት ግንባታው 33% ላይ ይገኛል::
– የግብርና ምርት ማዕከላት (የለሚ ኩራ ወረዳ 2 ሀያት፤ ወረዳ 5 እና ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 7 ቤተል ሳይትና የአቃቂ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት) ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል
– የሴቶች ተሃድሶና የአቅም ግንባታ ማእከል ግንባታው ተጀምሯል
– የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽን እና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ 70% ላይ ይገኛል
– በለሚኩራ ክ/ከተማ በአይነቱ ልዩ እና ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነው የለሚ ፓርክ ግንባታ በ7ዐ/3ዐ የመንግስትና የግል አጋርነት ግንባታው ተጀምሯል፡፡