በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አስተባበሪነት ከከተማ የተውጣጡ የሴት አደረጃጀት አባላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በለገሱበት ወቅት እንደገለጹት አሸባሪው የህውሃት ቡድን በትግራይ ሴቶች እና ህጻናት ላይ እያደረገ ያለውን ግፍ እና ሰቆቃ እንዲያቆም በቃህ በማለት ድምጻቸውን ማሰማት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በደም ልገሳ ላይ የተሳተፉ ሴቶች የኢትዮጵያን ሰላም በማስጠበቅ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎችን በምንችለው አቅም ለማገዝ የምንናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የአዲስ አበባ ሴቶችን የሚወክሉ አደረጃጀቶች በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊት በሁለት ዙሮች ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መላኬ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡