የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ በተለያዩ የከተማችን አካባቢዎች በተጀመረው የእሁድ ገበያ በተሻለ ሁኔታ ምርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርም ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል::
በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ የተቋቋመው ግብረሃይል ጠንክሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የህዝባችንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ተጨማሪ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል::