በዚህም መሠረት አንድ ኪሎ ጤፍ ከ50 እስከ 56 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
በከተማችን በሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት እና የተለያዩ 10 የመሸጫ አካባቢዎች ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ የእህል እና የግብርና ምርቶች ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል::
ለገበያ ከቀረቡት የእህል ምርቶች መካከል ጤፍ ፣ ስንዴ ፣ በቆሎ እና ገብስ በብዛት ወደ ገበያ የገቡ ሲሆን የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶችም ይገኙበታል።
የእህል አቅርቦቱ በኦሮሚያ ነጋዴዎች ዩኒየኖች በኩል የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ የገበያ ትስስር በመፍጠር እጥረቱና የዋጋ ውድነቱ እስኪቀረፍ ድረስ አቅርቦቱ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ምክትል ፕረዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ በከተማዋ የተፈጠረው የጤፍ ዋጋ መወደድ በአንዳንድ ነጋዴዎች የተፈጠረ ነው ያሉ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመነጋገር ምርት ማቅረቡን ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የዋጋ ንረቱን ለማባባስ ምርት በሚደብቁ እና ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።