በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በልዩ ድጋፍ የተከናወኑ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የአገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ቀልጣፋ የማድረግ ስራ፣ የከተማ ግብርና ስራዎች፣ የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ የሚያስችል የንግድ ሪፎርም ውጤታማ በማድረግ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥርና እርምጃ መውሰድ፣ የሎኮስት የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የአካፋይ መንገዶች የማስዋብ ስራ እና የጸጥታ ስራን ለማጠናከር በህዝባዊ ሰራዊቱ የሚከናወን የቀንና የማታ ሮንድ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአጠቃላይ ሰው ተኮር የሆኑ የተለያዩ የልማት ስራዎች ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።
በተጨማሪም ባለፉት 60 ቀናት በልዩ ሁኔታ ታቅደው ከተተገበሩት ተግባራት መካከል የክፍለ ከተማው አስተዳደር ህንጻ ግንባታ ስራ በተለያዩ ምክንያቶች ቆሞ የነበረውን ሲሆን የህንጻ ግንባታ ስራውን ለማጠናቀቅ ያሉበትን ችግሮች በመፍታትና ግንባታውን በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ማድረግ ነበር።
በዚህም መሠረት የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲያገኙ በሚያስችል መልኩ የአስተዳደሩ ህንጻ ተጠናቆ በነገው ዕለት የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል።
ከአስተዳደሩ ህንጻ ምርቃት በተጨማሪም ባማረ መልኩ ተገንብቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው የምገባ ማዕከል፣ ውብ እና ማራኪ ተደርጎ የተገነባው የ “ላፍቶ ፓርክ” እና የተለያዩ አደባባዮች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል።