ህንፃው ለከተማችን ቅርስ ብቻ ሳይሆን ትውልድ የሚጠብቀው ዘመን ተሸጋጋሪ ውድ ሃብት ነው፡፡ለህዝባችን ከዚህም የላቀ ዘመናዊ የአገልግሎት መዳረሻዎች ይገቡታል፤ ተባብረን ይህንን ስራ እውን እንዳደረግን ተባብረን የኢትዮጵያን ትንሳኤም እናረጋግጣለን!!
በዚህ ታሪካዊ ስራ የተሳተፋችሁ ባለሙያዎች ተቋራጮች ፣ አማካሪዎች ፣አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን ከአክብሮት ጋር ለማቅረብ እወዳለሁ!!
ጀመርን እንጂ አላጋመስንም፤ ሩጫችን ከግባችን ሳይደርስ አይቀዘቅዝም ፤ ዛሬን ሳይሆን ነገን እያሰብን ከህዝባችን ጋር ብዙ ሪባኖችን መቁረጣችንን እንቀጥላለን፡፡
ገና ብዙ ለመስራት መንፈሳችንም ልባችንም ሙሉና ዝግጁ ነው፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ