የዓለም የእግር ኳስ ውድድር በህዳር 2022 በኳታር ከመካሄዱ በፊት የፊፋ ዋንጫ የዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራት ጠቅላላ በ51 አገራት ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን የመጀመሪያው መዳረሻ ኢትዮጵያ ሆናለች። ለሦስተኛ ጊዜ በሀገራችን የመጣው ይህ ዋንጫ በግንቦት 16 በአዲስ አበባ እንደገባ ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቤተ መንግሥት ቀርቧል። በወርቅ የተሠራውን 6.1 ኪሎ የሚመዝነውን ዋንጫ ለመንካት የሚፈቀድላቸው ርዕሰ ብሔሮችና ውድድሩን ያሸነፈው ቡድን አባላት ብቻ ነው።
ፕሬዚደንቷ በንግግራቸው “የእግር ኳስን“ሰዎችን በአንድ ላይ በማምጣት፣ አንድ በማድረግ፣ ለአንድ ዓለማ በማሠራት፣ የጨዋታውን ሕግ በማስከበር፣ እርስ በርስ በማከባበር፣ በአንድ ሜዳ ላይ በመጫወት እጅግ ጠንካራ ፋይዳ ያለው መሳሪያ ነው” ሲሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም “ይህንን ዋንጫ በእጄ ለመያዝ እድል ለመላው ኢትዮጵያን የተሰጠ እድል ነው … ተስፋ ይሰጣቸዋል … ይህንን ለማየት እድል የሌላቸውን በጽኑ አስበቸዋለሁ” ብለዋል።