ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የታሪክ ተመራማሪ እና ደራሲ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለአመታት በታሪክ እና በስነፅሁፍ ዘርፍ ሀገርን እና ትውልድን በትብብር መገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን በመሰራት ላይ ይገኛሉ ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቢሮዋቸው ተገኝተው ላበረከቱት የመፅሐፍት ስጦታ እና ለነበራቸው ፍሬያማ ውይይት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እውነተኛው የዘር ምንጭ በሚል የጻፉትን መፃህፍት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እናደርጋለን ብለዋል ወ/ሮ አዳነች። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ በበኩላቸው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቢሮአቸው ላደረጉላቸው መልካም አቀባበል አመስግነዋል።