የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ለጀግናዉ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ21.5 ሚሊዮን ብር በላይ በዓይነትና በብር ያሰባሰበዉን ሀብት አሰረከበ፡፡
የክፍለ ከተማው አስተዳደር መላዉን የክ/ከተማዉን ነዋሪዎች በማስተባበር በአጭር ቀን ዉስጥ ለሀገርና ለህዝብ የህይወት መሰዋዕት እየከፈለ ለሚገኘዉ ጀግናዉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማሰባሰቡን ገልጹዋል፡፡
በዓይነት ከተሰበሰቡት ዉስጥ 50 ሰንጋ በሬ ፤ 186 በግ፤ 22 ፍየልና ደረቅ ምግቦች አካቶ ያሰባሰበ ሲሆን በጥሬ ገንዘብ ከ16.4 ሚሊዮን ብር በላይ ስብሰቧል፡፡
አስተዳደሩ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን በዚህ ዙር ነዋሪዉ ያደረገዉን ተሳትፎንም ምስጋና አቅርቧል፡፡