በአንጋፋው አርቲስት አለማየሁ እሸቴ የክብር ሽኝት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ፤ ኢትዮጵያን ሳይሰስት ያገለገለውን፤ የጥበብ ሰዉ ነው ብለዋል ።
አለማየሁ እሸቴ ሀገሩን በቅንነት በማገልገለ፣ በታልቅ ፍቅር በመትጋት እና ዘመን ተሻጋሪ ስራ የሆኑ በርካታ የጥበብ ስራዎችን የስራ ኢትዮጵያዊ ነው ያሉት ምክትል ከንታባዋ በአካል ቢለየንም በስራዎቹ ከመቃብር በላይ እየታወሰ፣ እየተዘከረ እና እየተመሰገነ ብልባችን ህያው ሆኖ አብሮን ይኖራል ብለዋል ።
የከተማ አስተዳደሩ በቅንነት ፣ በትጋት እና በታማኘነት ያገለገሉትን ከፍ በሚያደርግበት በዛሬው ቀን ሀገርና ህዝብን ማገልገል ያስከብራል እና አርቲስት አለማየሁን በታላቅ ክብር መሸኘቱን ገልጸዋል ።
“አዲስአበባ ቤቴ” የሚለውን የብዙዎች የናፍቆት ማስታገሻ የሆነዉን የጥበብ ስራ ተገቢዉን ክብር በመስጠት በቀጣይ እንደሚሰራበት ወ/ሮ አዳነች ጠቁመዋል ።
ለቤተሰቦቹሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙያ አጋሮቹ እንዲሁም በአገር ዉስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙ አድናቂዎቹ በራቸው ፣ በከተማ አስተዳደሩና በነዋሪዎች ስም ልባዊ መፅናናትን ተመኝተዋል ።