የአሸባሪዎቹ የህወሃትና የሸኔ ተላላኪዎች እንደተለመደው ከፊታችን ባሉት ቀናት የሚከበሩትን የመስቀልና የኤሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባ ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በህብረተሰቡ እና በፀጥታ ሃይሉ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ዩኒሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተደረገ የኦፕሬሽን ስራ
1. ህገወጥ የብሬን ጦር መሳርያ ከነተጠርጣሪው
2. 1 ክላሽ ከ86 የክላሽ ጥይት ጋር
3. 2 ስታር ሽጉጥ
4. 16 የስታር ሽጉጥ ጥይት
5. 7 የክላሽ ካርታ ከ4 ተጠርጣሪዎች ተይዘው በፖሊስ ምርመራ ስር ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አንድ ግለሰብ ጾታውን ሴት አስመስሎ አለባበሱን በመቀየር ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ትላንት ምሽት 3:00 አካባቢ አፍራን ሆስፒታል አከባቢ አንድ ጾታውን ሴት አስመስሎ አለባበሱን በመቀየር ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ የፀጥታ ሀይሉ ከህዝቡ ጋር በመቀነጀት በቁጥጥር ስር ውሎ ፖሊስ ምርመራውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ሁለቱን መረጃዎቸ ከክ/ከተሞቹ ኮምዩኒኬሽን ፅ/ቤቶች የወሰድነው ነው፡፡
እነኚህ እኩይ ሃይሎች በከተማችን ሊፈፅሙት ያቀዷቸው የተለያዩ የሽብር ድርጊቶች የሰላም ዘብ በሆነው ህዝባችንና የፀጥታ ሃይሉ የተቀናጀ እንቅስቃሴ በፍፁም ሊሳካ የማይችል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡
ህብረተሰቡም መጪዎቹን በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ከወዲሁ በተደራጀ መልኩ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ፤አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለፀጥታ ሃይሉ ፈጥኖ እንዲያሳውቅ ከወዲሁ ጥሪ እናስተላልፋለን