የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዕለት ኑሮን ለመግፋት የሚቸገሩና በኑሮ ውድነት እየተፈተኑ የሚገኙ ዜጎችን ጫና ለማቃለል በአንድ ወር ውስጥ ተገንብተው የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርጓል።
3 የዳቦ ማምረቻ ማዕከላትን ጨምሮ የአቅመ ደካማ ዜጎች ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የተጀመሩት መርሀ ግብሮቹ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ባለሀብቶች በተሰበሰበ 57 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የሚገነቡ ናቸዉ።
በባለሀብቶቹ ድጋፍ የሚተከሉት 3 የዳቦ ማምረቻ ማሽኖች በቀን 25 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ይኖራቸዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ባለሀብቶቹ በገቡት ውል መሰረትም ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተጨማሪ 30 ሺህ ዳቦን በማምረት ለክፍለ ከተማው ያቀርባል።
በ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪም የአቅመ ደካማ ቤቶችም የሚገነቡ ይሆናል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፡- ከገንቢዎቹ ጋር ተፈራርመው ስራውን ያስጀመሩ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉም ተብሏል።