========================
(አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የከፈተውን 3ኛ ዙር ጦርነት ለመመከት በግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የመከላከያና ጥምር ጦሩ የሚውል 1.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለመከላኪያ ሰራዊትና ለጥምር ኃይሉ ለሁለተኛ ዙር ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አስረክቧል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አበራ ብሩ እንደገለጹት በተያዘዉ በጀት ዓመት በክፍለ ከተማው የሚገኙ ባለሃብቶችን፣ ተቋማትና ነዋሪዎችን በማስተባበር በገንዘብ እና በአይነት ለመከላከያ ሠራዊት 1.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለትም በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሁለተኛ ዙር 30 በሬ፣ 73 በግ፣ 35 ኩንታል በሶ፣ 33 ኩንታል ዳቦ ቆሎ፣ 26 ኩንታል ድርቆሽ፣ 600 ኪ.ግ ስኳር፣ 20 ኩንታል ዱቄት፣ ቴምር 36 ካርቶን፣ ፖስታ 800 እሽግ፣ 50 ፍራሽ እና ሌሎች ግብአቶች ተሰብስቦ በ6 መኪና ተጭኖ ለሀገር መከላኪያ ሰራዊትና ለጥምር ኃይሉ ድጋፍ ማስረከብ መቻሉን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል ።
የተሰበሰበዉን ሀብት ያስረከቡት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በአጭር ጊዜ ዉስጥ የተሰበሰበዉ ሀብት ህዝቡ የሀገራችን ህልዉና ለማረጋገጥ ዋጋ እየከፈለ ያለዉ ለመከላከያ ሠራዊታችኝ ደጀን ለመሆንና ለመደገፍ ያለዉን ቁርጠኝነት ያሳያል በማለት መላው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ሀገርን ለማዳን ውድ ሕይወቱን እየሰጠ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ሰራዊቱን ከመቀላቀል ጀምሮ በዓይነትና በገንዘብ የሚደረገው ድጋፍም አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸዉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።