የነባሩ አሮጌው የአቃቂ ድልድይ በዋናነት የሚያገናኛቸው የቃሊቲ ቶታል እና አቃቂ ከተማ እንዲሁም የኮዬ ፍጬ እና ቂሊንጦ አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ መሸጋገሪያ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡
ሆኖም እያደገ ከመጣው ከፍተኛ የትራፊክ መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ ነባሩ ድልድይ ለእግረኛም ሆነ ለአሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ምቹ ባለመሆኑ ዘመናዊና ደረጃውን እና ጥራቱን የጠበቀ ድልድይ ግንባታ ይከናወናል፡፡
አዲሱ ግንባታ
• 61.2 ሜትር (በድልድዩ መነሻና መድረሻ በኩል በድምሩ 140 ሜ ወደ ድልድዩ የሚያገናኝ መንገድ ግንባታ አካቷል)
• 25 ሜትር የጎን ስፋት አለው
አዲስ አበባን በሁለንተናዊ መልኩ የመለወጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!