በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ሻማችን ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ለተሰዉ መከላከያ ሰራዊታችን” በሚል የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ተከናወነ ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት የአባቶቻችን የድል አድራጊነት ታሪክ በእኔና በእናንተ ይደገማል እንጂ አይበላሽም፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ታሸንፋለች በማለት ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ሰራዊትየጀግኖች ጀግና መሆኑን የገለጹት ክብርት ከንቲባዋ አይደለም አሸባሪው የህወሓት ቡድን ጁንታ በዘመናዊ መልክ የጦር መሳሪያ የታጠቁትን የመከተና ያባረረ የአባቶቻችን ልጆች ነን ሲሉ ተናግረዋል ።
መላው የከተማዋ ነዋሪም ተደራጅቶ አከባቢውን በመጠበቅ ማንኛውንም አይነት የክፋት ተግባር ለጸጥታ አካላት በማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ከደጀን እስከ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊትን ጎን እንዲሰለፍም ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ለኢትዮጵያ ሀገራችን የመስዋዕትነት መስዋዕት ለመክፈል የተዘጋጀን ሠራዊት ነን ያሉት ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያዊ በባርነት የመኖር ታሪክ የለውም፤ ባንዳ ምን ጊዜም ባንዳ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
አከባቢህን ጠብቅ!
ወደ ግንባር ዝመት!
መከላከያን ደግፍ!