ይህ አለም አቀፍ የጥፋተኞች አያያዝ መስፈርትን ያሟላና ወጣቶች ስራ ወዳድነትን እንዲሁም የስፖርትና የመዝናኛ ለወጣቶቹ ሁለንተናዊ ግንባታ የሚያግዙ ጉዳዮች የተካተቱበት ማእከል ግንባታ ከተማ አስተዳደሩ በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለፍሬ በቅቷል፡፡

20,186.42 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አርፏል

6,000 ካሬ ሜትር ቦታ በአረንጓዴ ቦታ ተሸፍኗል

2,892 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የከተማ ግብርና ስራ ተሰርቶበታል

4364.53 ካሬ ሜትር ቦታ በውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ተሸፍኗል

በአጠቃላይ 1,213.38 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ 2 የወንዶችና የሴቶች ስፖርት ሜዳዎች ተሰርተውለታል

ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 17 ብሎኮች ሲኖሩት የአስተዳደር ህንፃ፣የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተ መፅሐፍት፣መመገቢና ማብሰያ ክፍሎች፣ክሊኒክና የምክር አገልግሎት መስጫ ክፍል፣ዎርክሾፕ፣የጠያዎች ማረፊያ፣3 የወንዶችና 2 የሴቶች ዶርሚተሪ፣ላውንደሪ፣ሁለገብ አዳራሽ እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል፡፡