ከእነዚህ እርጃዎች መሃከል የዋጋ ማረጋጋት ግብረ ሃይል ተደራጅቶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቂ አቅርቦት ለከተማዋ እንዲኖር በማድረግ፤ እንዲሁም የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር ክትትልና ሕግ የማስከበር ስራዎችን የሚያከናውን ይሆናል፡፡
በመሆኑም በአሁን ሰዓት ከአጎራባች አካባቢዎች በርካታ መጠን ያለው ምርት ወደ ከተማዋ መግባት ጀምሯል::
ለተከታታይ ቀናትም በእሁድ ገበያ ( ጎዳና ላይ)ና የሸማች ማህበራት በኩል በስፋት የሰብል ምርቶችንና የተለያዩ አትክልት እና የእንስሳት ውጤቶች ለህብረተሰቡ በየአካባቢው እየቀረበ ነው ፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ የተለያዩ የሰብል ምርቶችን፤ ዘይት: የቁም እንስሳቶችና የእንስሳት ተዋፅኦዎችን እንዲሁም የአትክልት ውጤቶችን ከአምራቾች በቀጥታ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ በመሆኑ በአካባቢው በሚገኙ የሸማች ማህበራት ሱቆች እና ከእሁድም ባሻገር ባሉት ቀናት በእሁድ የገበያ ቦታዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን።