👉 ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሩ በ 3 ሄክታር ይዞታ ላይ የተገነባ ሲሆን 510 ቤቶችን የያዙ16 ብሎክ ዘመናዊ አፓርትመንቶች ያሉት ነው።
👉 የቤቶቹ የግንባታ ቴክኖሎጂ የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከተለመደው የሕንጻ ግንባታ ለየት የሚያደርገው ጥራትን እና ፍጥነትን ያማከለ ብክነትን የሚቀንስ የአሰራር ስልት በመከተሉ ነው ፡፡
👉 ቤቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 1 ዓመት ከ6 ወራት ብቻ እንደወሰደ ተነግሯል።
👉 የቤቶቹ ዓይነት የስካይ ቪላ ዱፕሌክስ እና የአፕርትመንት ቤቶችን ሲሆኑ ከ150 ካሬ ሜትር እስከ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ናቸው።
👉 የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም ያለው የመኪና ማቆሚያ ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ ጂሚናዚየም፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የአረንጓዴ ቦታና መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር የያዘ ነው።
👉 ከዚህ በተጨማሪ ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ፣ የስፖርት ሜዳ ፣ የልጆች መጫዎቻ ቦታና የመዋኛ ገንዳ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አሟልቶ የያዘ ዘመናዊ መንደር ነው፡፡