ለሃገራችን አንቱ የተሰኙ ባለሙያዎችንና ታላላቅ ሰዎችን ሲያፈራ የኖረው አንጋፋውና የሃገር ባለውለታው የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት የ80ኛ አመት በአሉን ማክበር በመቻሉ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብና ቤተሰብ በአጠቃላይ እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ለማለት እወዳለሁ!!
ይህንን የካበተ አቅሙን በላቀ ሁኔታ ለመጠቀምና የትውልድ ግንባታ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚሁ ቀን የከተማ አስተዳደራችን አዳዲስ ህንፃዎችን በመገንባት ማስመረቅ ተችሏል፡፡ አሁንም የተከበረውን የቴክኒክና ሙያ ክህሎት ስልጠና ተቋሞቻችንን በማጠናከር የኢትዮጵያን ብልፅግና በኢትዮጵያ እጆች እውን የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!