ሚያዚያ 10/2014 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
መንግሥት የህዝቡን ችግሮች ለመፍታት ከህዝብ ጋር ውይይት እንዲደረግ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በውይይቱ ወቅት በሰላምና ፀጥታ ችግሮች ዙሪያ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል የጋራ ግብረሃይል ማቋቋም ማስፈለጉ ተገልጿል።
ግብረ ሃይሉ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ ሲሆን የጋራ ዕቅድ በማዉጣት ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል የቢሮ ኃላፊና የፀጥታና መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ፍሰሐ ጋረደው ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም በማዕከል ደረጃ የተቋቋመው ይህ ግብረ-ሃይል በየጊዜው የከተማውን የሰላምና የፀጥታ ችግሮች እየገመገመ አፈፃፀሙን ሪፖርት የሚያደርግና ከ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ምክረ ሃሳብ በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የአፈፃፀም ዝርዝር መርሃ ግብር ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ፣ እንዘጋጅ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼