የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በከሰዓት ውሎው የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበት በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።ቀጥሎም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ፍ/ቤት፣በአቃቤ ህግ ቢሮና በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች በረዳት ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ በስራቸው ታታሪና ምስጉን የነበሩ ዳኞችን በመለየት ለይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በእጩነት አቅርበዋል።
በዚሁ መሠረት 5 እጩ ዳኞችን ለአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተሾሙ ሲሆን 16 ዳኞችን ደግሞ ለአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሹመዋል። በተጨማሪም ለአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተርነት አቶ አመንቲ መቻሉንምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በዝርዝር ካየ ኋላ ሹመታቸውን በማፅደቁ ቃለ መሀላ እንዲፈፅሙ ተደርጓል።በመጨረሻም በመደበኛ ጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎችን በማጠቃለል በም/ቤቱ አፈጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቶ ጉባኤው ተጠናቋል።