ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው የፌደራል የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩትንና የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑትን የወ/ሮ ሀቢባ ዑመርን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው!!
ፍትህ ሚኒስቴር ለከተማው ም/ቤት ባቀረበው ይፋዊ ጥያቄ መሠረት በግለሰቧ የተሰጣትን የመንግስትና የህዝብ ሀላፊነት ወደጎን በማለት በክ/ከተማው በአርሶ አደርና አርሶአደር ልጅ ሰበብ በተፈፀመ የመሬት ምዝበራ ተጠርጥረው መሆኑ ተገልጿል።