የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና ቀልጣፋ ለማድረግ በሶስት ክፍለ ከተሞች እና በ18 ወረዳዎች አገልግሎታችን በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራን አስጀምረናል፡፡ እንዲሁም የዘጠኝ ስማርት ወረዳዎች ግንባታቸው ተጠናቆ አስፈላጊው ግብአት እንዲሟላላቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎን የህዝብ አቤቱታና ቅሬታዎችን ምላሽ ለመስጠት በሰራነው ስራ ከቀረቡ 4‚542 አቤቱታዎችና ቅሬታዎች ውስጥ 3‚104 የሚሆኑት የተፈቱ ሲሆን ቀሪዎቹ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል ።
የከተማዋን ሰላምና ደህንነት የሚያዉኩ እኩይ ተግባራትን፤ ከደንብ መተላለፍ ጀምሮ ከተለያዩ ወንጀል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን መመከት የሚያስችል አደረጃጀቶች ተፈጥሯል በተለይም የሰላም ምክርቤትን በማቋቋም፣ ህብረተሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን የማድረግ፤ በፀጥታ መዋቅሩ 4,300 የሚሆኑ ምልምል ፖሊሶቸንና 2,674 የደንብ ማስከበር አባላት አሰልጥነን ወደ ስራ የማስገባት እንዲሁም ፖሊስ ጣቢያ ያልነበራቸው 60 ወረዳዎች የፖሊስ ጣቢያ እንዲኖራቸው የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
የትምህርት አቅርቦትና ፍትሐዊነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ 219‚456 እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ መደበኛ ትምህርት እንዲገቡ ተደርጓል ፤ በተመሣሣይ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ንጥር ተሳትፎ እንደ ቅደም ተከተሉ 88.5 % እና 65.7% ደርሷል፡፡
የትምህርት ቤት ቁሳቁስ አቅረቦት ጋር በተያያዘ፣ 233 የምገባ አዳራሾችና 1,721 የመማርያ ክፍሎች ተገንብተው ለ600 ሺህ ተማሪዎች በቀን ሁለት ግዜ በመመገብ ለመማር ማስተማሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በውጤቱም በ12ኛና በ8ኛ ክፍል እንደ ሀገር ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል፡፡
በጤና አገልግሎት በኩል መከላከል ላይ የሚሰራው ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ አክሞ ማዳን፤ተደራሽነት እና የጥራት ጉዳይም ትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ አንፃር የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ ጫና የሆነውን የኩላሊት እጥበት ችግር ለመፍታት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሆፒታሎች የኩላሊት እጥበት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በሆሰፒታሎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን የወረቀት አልባ አገልግሎት ጀምሯል፤በተጨማሪም እናቶች ላይ ሊከሰት የሚችለውን ህመምና ሞት ለመቀነስ ከ400 በላይ አልጋ የሚይዝ ወረቀት አልባ፣ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖረው የተደረገው የአበበች ጎበና የእናቶች እና ህፃናት ዘመናዊ ሆስፒታልን ገንብቶ ወደ ስራ በማስገባት የእናቶችን የወሊድ ወቅት ህመምና ስቃይ ለመቀነስ የማስቻል ስራ ተሰርቷል፡፡
በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የውጪ የህክምና ጉዞን በማስቀረት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አምስት ዘመናዊ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግንባታ ለማሳደግ የሮሀ ህክምና ማእከል ፤ የኢጋድ ቀጠናዊ የካንሰር ልህቀት ማእከል የላፍቶና ቤቴል መንዲዳ ሆስፒታሎች ግንባታ ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎች በመገንባት አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በበጎፈቃድ አገልግሎት ስራችን መረዳዳትና አብሮነት የተጠናከረበት በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል መልኩ በከተማችን ከ2,ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና ደጋፊ የሌላቸው የከተማችን ነዋሪዎችን የመደገፍ ከ 591 ሺህ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማእድ በማጋራትና ከ2 ሺህ በላይ የድሃ ቤቶችን በማደስ ደሆችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በቀን አንድ ግዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎቻችን ለመመገብ አምስት የምገባ ማእከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን፤ የስድስተኛውም ማእከል ግንባታ ተጠናቋል፡፡
ከ8ሺህ በላይ የጎዳና ልጆች በማንሳት ከ3ሺህ በላይ የሆኑትን ወደ ስራ እንዲሰማሩ የተቀሩትን ደግሞ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘትና የተለያዩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ተደርጓል፡፡
በስፖርት ዘርፉ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ራስ ሀይሉ የውሃ ገንዳ፤ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ጨፌ ሜዳ፤ አፍንጮ በር ሁለገብ ሜዳና በጥቅሉ 51 የስፖር ማዘውተርያ ስፍራዎች ተገንብተው ላገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡
ወጣቶችን እና ሴቶችን በስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በበጀት አመቱ ለ345 ሺህ 062 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 262,843 ሺህ የሚሆኑት ቋሚ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፤ 82 ሺህ 189 የሚሆኑት ደግሞ ጊዚያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ናቸው፡፡
ባለፉት ሶስት አመታት በአምስቱ የእድገት ተኮር ዘርፍ ላይ ሲሰሩ የነበሩ 315 ኢንተርፕራይዞች ወደ ታዳጊ መካከለኛ ባለሃብትነት ተሸጋግረዋል፡፡
በሶስት ዙሮች በከተማችን ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት በምግብ ዋስትና እና በልማታዊ ሴፍትኔት መርሃግብር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በመጀመርያዉ ዙር ለ29,410 ነዋሪዎች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚ በመሆን ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል ።
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ገበያ ማዕከላትን በማበራከት፤ የምርት አቅርቦት በብዛት እንዲቀርብ ያስቻለ ግማሽ ቢሊዮን ብር ለሸማቾች በማቅረብ በአምራቾች እና በሸማቾች መካከል ዘመናዊ የችርቻሮ አውታሮች በማስፋፋት እና የግብይት ሰንሰለቱን በመፍጠር የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡
የከተማችንን ነዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የሚስፈልገው የመደበኛና የካፒታል ወጪ ለመሸፈን ባለፉት አስራ አንድ 47.1 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፤ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ6.8 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡
በከተማችን የተስተዋለው ህገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል በልዩ ትኩረት ግብረ-ሃይል በማቋቋም በህገወጥ መንገድ የተያዘን ከ1ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለማቃለል ልዩ መመርያና የግምገማ ስርአት በመዘርጋት በመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ 430 ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ በመወሰን ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡
ከከተማዋ እድገት ጋር ተያይዞ የመጣውን የመሬት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት 40.34 ሄክታር መሬት ለመኖርያ ቤት ግንባታና 138 ሄክታር መሬት ሃገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶችና ለግል አልሚዎች በአስተዳደሩ ካቢኔ ወሳኔ መሰረት ማስረከብ ተችሏል፡፡
የመኖርያ ቤት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም በበጀት አመቱ እየተገነቡ ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሶስት ፓኬጆች የተከፈሉ ሲሆኑ፤ የ20/80 የፓኬጅ 2ኤ (13,064) 2ቢ (26,203) እና ፓኬጅ 3 (47,952) ቤቶች ግንባታ አፈፃፀማቸው እንደ ቅደም ተከተሉ 99.64%፤ 96.96% እና 94.93% ደርሷል፡፡ የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም በተመለከተ ፓኬጅ 2 (17,737) እና ፓኬጀ 3 (20,503) የግንባታ አፈፃፀማቸው እንደቅድም ተከተሉ 93.99% እና 83.60% ሆኗል፡፡
የመኖሪያ ቤቶችን ችግርን ከመሰረቱ ለመፍታት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተቋማት በጋራ ሽርክና በመፍጠር በቀጣዩ አምስት አመት አንድ ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡
ባለፉት አመታት የተገነቡት ላይ የሚታየው ኢፍትሃዊ አጠቃቀም በማጣራት በተገኘው ውጤት 1761 የቀበሌ ቤቶችን ለድሆች ተሰጥቷል ፤አንዳንዶቹንም ያሉበትን የኑሮ ደረጃ በማጤን ባሉበት ህጋዊ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን በማጥራት ሂደት የተገኙ የጋራ መኖርያ ቤቶች ለልማት ተነሺዎችና ለ1997 ዓ.ም ተመዝጋቢዎች በእጣ ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ ይገኛል ፡፡
በኮንስትራክሽን ዘርፉ ከ3ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ የማህበራዊና የኢኮኖሚ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀም በተመለከተ አድዋ ዜሮ ኪሎሜትር ቤተ-መዘክር ፕሮጀክት ፣የመዘጋጃ ቤት ህንፃ እድሳት ታላቁ ህዝብ ቤተመፃህፍት እና የታላቁ ቤተመንግስት መኪና ማቆሚያ ህንጻ ግንባታ በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ ።
ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት የማስዋብ ስራ ለከተማችን ውበትና ገፅታ ግንባታ ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ያላው ፕሮጀክት ማጠናቀቅ ተችሏል ።
ፕሮጀክቱ ከውብ ገፅታ በላይ በምድር ውስጥ ከ1ሺህ 400 በላይ ተሸከርካሪ ማስተናገድ የሚችል ስማርት ፓርኪይንግ፤ ሱቆችና መፀዳጃ ቤቶች አካቶ የተሰራ ሲሆን ለበርካታ ሴቶችና ወጣቶች ሰፊ ስራ እድል የሚፈጥር ነው፡፡
በአጠቃላይ በወቅቱ መጠናቀቅ ሲገባቸው ከዓመት ዓመት እየተንከባለሉ የመጡ በርካታ ፕሮጀክቶች ቢኖሩም የ2013 ዓ.ም የፕሮጀክት አፈፃፀማችን በፍጥነትም ሆነ በጥራት የመጨረስ የነበረውን ልምድ በእጥፍ ያሻሻለ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት እና ፍላጎትን ለማጣጣም እንዲሁም አገልግሎቱን ለማሻሻል አስተዳደራችን የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡
536 አውቶቢሶች በኪራይ ወደ ስምሪት ገብተው ከነበሩት ውስጥ የተሻለ አገልግሎት የሰጡትን በመለየት ዉል በማደስ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቀጥሉበመደረጉ ከአጭር ጊዜ አኳያ ችግሩን ለመቀነስ ጥረት ተደርጓል፡፡ ከረጅም ጊዜ አኳያ 3ሺህ አውቶቢሶችን ለመግዛት የታቀደ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ በጀት አመት የ300 አውቶብሶች ግዢ እንዲፋጠን ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከተማችንን ውብና ፅዱና አርንጓዴ ለማድረግ “እኔ የከተማዬ የፅዳት አምባሳደር ነኝ ” በሚል መሪቃል በየወሩ 600 ሺህ የሚደርሱ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአካባቢ ፅዳት ማሳተፍ ተችሏል፡፡ በደረቅ ቆሻሻ በማንሳት መልሶ መጠቀም እንፃር በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 35 ሺህ ቶን ወደ 50 ሺህ ቶን ከፍ በማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራት 141 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ችለዋል፡፡
የ2014 በጀት አመት የእቅድ አቅጣጫዎች በተመለከተም የቀጣይ አስር አመት መሪ እቅዳችን ተገቢው ዝግጅትና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተደርጎበት፣ የከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በዝርዝር የዳሰሰና ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለጠጡ ግቦችን እንዲይዝ ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡
ለከተማችን ነዋሪ በተዋረድ የሚሰጠው አገልግሎቶች ከምንግዜውም የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍናን በመጠበቅ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የመቅረፍ እና የግልፀኝነትና የተጠያቂነት አሰራሮችን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የሪፎርም ስራዎች የመተግበር ጉዳይ ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ይሆናል፡፡
የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነት በተደራጀ መልኩ የመፍታት ጉዳይ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ መስኮችን አሟጠን በመጠቀም ስራ የሌላቸው ዜጎች ወደ ስራ እንዲሰማሩ ይደረጋል ።
ዘመናዊ የመሬት ልማት አስተዳደር የመፍጠርና የማጠናከር ስራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ለልማት የሚውል መሬት በማቅረብ ልማቱን ማፋጠን ፤የከተማ መልሶ ማልማት ስራ ማጠናከር ፤ህገወጥ የመሬት ይዞታዎችን ስርእት ማስያዝና የመሬት መረጃ ካዳስተር ስርአቱን አጠናክሮ የማስቀጠል ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡
የከተማውን የትራንስፖርት ችግር ማቃለል፤ንፁህ የመጠጥውሃ አቅርቦት፤ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራሞና የጤና አገልግሎት የማሻሻል ሥራ በልዩ ትኩረት የሚሠራ ይሆናል፡፡
የፕሮጀክት አፈፃፀም ልምዳችንን በማጠናከር አዳዲስና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በመፈፀም አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡