በ8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ በምክር ቤቱ የፕሬስና ህዝብ ግነኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ አለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የሚገመግም ሲሆን ልዩ ልዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ አቶ አዲስ አለም ተናግረዋል፡፡