የከተማ አስተዳደሩ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያጋጠመው ችግር ለክልሉ ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ ለድርቅ ለተጋለጡ ወገኖቻችን የሚሆን ድጋፍ አድርጏል::
በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶችን እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል::
የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር በበኩሉ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጏል::
የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች በግንባር ቀደምትነት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል::