ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ለሆኑት ዶ/ር አብረሃም በላይ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።በርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ድጋፉ በጁንታው እኩይ ተግባር ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ የትግራይ እህት ወንድሞቻችን አፋጣኝ ምላሽ ለመጠት ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲ ህይወቱን የሰዋ ህዝብ በመሆኑ በነሱ የደረሰው ጉዳት የኛም ጉዳት በመሆኑ በቀጣይ ክልሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡የትግራይ ክልልን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ተረድቶ ለህዝቡ ያለውን አለኝታነት በመግለጹ በህዝቡ ስም አመስግነዋል ፡፡በድጋፉም 2ሺህ ኩንታል ጤፍ፣2ሺህ ኩንታል ስንዴ እና 2ሺህ ኩንታል በቆሎ በጠቅላላው 18.3 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡