ቢሮው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ለሕዝባዊ ሰራዊት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በዛሬው እለት መስጠት ጅምሯል።
ሕዝባዊ ሰራዊቱ የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር የሚያደርገውን አስተዋጽኦ በዘላቂነት ለማስቀጠል ስልጠናው መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጽጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነአ ያደታ ያለሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ሕብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አስታዉቀዋል፡፡
የአዲስ አበባን ከተማ ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባን ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ለሰላሙ ዘብ በመቆም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ያሁኑ ስልጠናም የተጀመረዉን የሰላም መጠበቅ ተግባር የበለጠ እንደሚያጠናክረዉ ይታመናል፡፡
ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!