የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክትን አስፈላጊውን መሰረተ ልማቶች አሟልቶ ለማስረከብ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የA-አይነት የዶሮ ጎጆዎች፣መመገቢያ እና አውቶማቲክ ውሀ መጠጫዎች፣ጋልቫናይዝድ ሽቦ ሳጥኖች እና የመመገቢያ ገንዳዎች እንዲሁም RHS መወጠሪያና መቆሚያ ምርቶች እየተመረቱ ይገኛሉ፡፡
የዶሮ ዕርባታው እያንዳንዱ ዩኒት 160 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን የሚይዙ 297 ዩኒቶች የሚኖሩት ሲሆን በዚህም አጠቃላይ 47,250 ዶሮዎችን የመያዝ ዓቅም አለው፡፡
በማዕከሉ የእንቁላል ዶሮዎች ሼዶችን ጨምሮ የወተት ለሞች እና የእርድ የከብቶች ማደለብያ በአጠቃላይ 38 ሼዶች እንዲሁም 40 የምርት ማሳያ ሱቆች ተገንብተው ተጠናቀዋል፡፡