ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ለሀገር መከላከያ ሚንስትር ዶ/ር ቀነአ ያደታ አስረክበዋል ።
በተጨማሪም ለአባት አርበኞች ፣በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን ላጤ የህክምና ባለሙያዎች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ የበዓል ስጦታ ተሰጥቷል።
የከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ለክልል ልዩ ሃይሎች እና የጸጥታ አካላት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጥሬ ገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡