በቦሌ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፤ ከደንብ ማስከበር ፤ ከንግድ ፅ/ቤት፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅንጅት በመሆን በተሰራ አዋኪ ድርጊት የማስወገድ የግብረሀይል እንቅስቃሴ :-
👉 ቴክሳስ ላውጅ ተብሎ በሚጠራው ንግድ ቤት የተገኘ 24 የሺሻ ዕቃ
👉 ግሮቭ ላውንጅ ተብሎ በሚጠራው ንግድ ቤት የተገኘ 50 የሺሻ ዕቃ
👉 ሴክሬት ላውንጅ ተብሎ በሚጠራው ንግድ ቤት የተገኘ 50 የሺሻ ዕቃ
# አጠቃላይ በ3ቱም የንግድ ቤቶች እርምጃ ተወስዶ 124 የሺሻ ዕቃ የተገኘ ሲሆን ቤቶቹንም የማሸግ ስራ ተሰርቷል::
ይህ ህገወጥነትን የመከላከል ስራ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።