የከተማ ኣስተዳደሩ ከለሚ ኩራና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች ያስባሰብውን ሃብት ከንቲባ አዳነች አበቤ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረክበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክልሉ የደረሰው ጉዳት ጉዳታችን መሆኑን በመገንዘብ አንድ ጊዜ ደግፈን የምንተወው ሳይሆን ሁሌም ከጎናችሁ ነን ብለዋል።
በቀጠይም በጦርነቱ ችግር የደረሰባቸው ወገኖች ለማቋቋም ክልሉ በሚያደረገው ርብርብ የከተማ አስተዳደራችን ድጋፋ አይለያችሁም ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች በክልሉ ውድመት የደረሰባቸው ሆስፒታሎች በሙያተኞች እና በግብዓት የመደገፍ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለክልሉ ከዚህ በፊት ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።
ችግሮችን የምንቋቋመው በጋራ ስንተባበር ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክ/ከተማና ን/ላ/ክ/ከተማ ዛሬ የተረገውን ድጋፍ ላሳተባበሩ አመራሮች፡ ባለሃብቶችና ግለሰቦች አመስግነዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፍለ የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ያደርገው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በክልሉ በወራራው የደርሰውን ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ከፍተኛ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በወራራው የወደሙ ት/ቤቶች መልሶ እንዲገነቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።