በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ለሚደርሱ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሁሌም ቀድሞ የሚደርሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ህዝብ ዛሬም 50 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ እህሎችን እና አልሚ ምግቦችን ለኮንሶ ወገኖቻችን ልኳል ብለዋል::
ይህ በጎ ሃሳብ እንዲሳካ እጆቻቸውን የዘረጉ ባለሃብቶችን በወገኖቻችን ስም እናመሰግናለን::