የከተማው አስተዳደር ከከተማው ህዝብ ያሰባሰበውን 291 ኩንታል በሶ፤ 157 ኩንታል ዳቦ ቆሎ ፤194 በሬዎችና ፤ 532 በጎች ፤ 9949 የቆዳ ሸበጥ ግብዓቶች በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት አስረክቧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በርክክብ ኘሮግራሙ ላይ አንደተናገሩት፣
“መከላከያ ሰራዊታችን ብሄራዊ ኩራታችን ነው፣ መከላከያ የሚሰጠን ውድ ስጦታ የሚተካ ስጦታ አይደለም። አይዟችሁ፣ ከጎናችሁ ነን ለማለት ነው ይህንን ስጦታ ያበረከትነው” ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ ለውድ ሀገሩ የሚከፍለው ህይወቱን ነው ያሉት ክብርት ከንቲባ አዳነች፣ ከተማ አስተዳደሩ ምንጊዜም ከመከላከያ ጎን ነው በማለት ገልፀዋል።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚስቴር ሚንስትር እና የመከላከያ ሰራዊት የሀገር አቀፍ የሎጀስቲክስና ገቢ አሰባሳቢ ብሄራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው፣ በአሸባሪው ህወሃት የተከፈተብንን ጦርነት ለመቀልበስ ፊት ለፊት ውድ ህይወቱን እየከፈለ ያለለውን ሰራዊት ለማበረታታት ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል