ከክፍለ ከተሞች የተሰበሰቡትን ሰንጋዎች በምክትል ከንቲባ መዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ኢዮጂ እና ሌሎች ከፍተኛ ጀነራሎች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ መዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት የአዲስ አበባ አስተዳደር በመጀመሪያው ዙር ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ ድጋፎችን በአይነትና በገንዘብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በሁለተኛው ዙር ደግሞ እስከ ነሐሴ 30 ባለው ጊዜ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፎችን ከህብረተሰቡ በማሰባሰብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ኢዮጂ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እያደረጉት ያለው ድጋፍ ሰራዊቱን ከማጠናከሩ ባለፈ የሞራል ስንቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙቀት ታረቀኝ ክፍለ ከተማው የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር እየተደረገ ባለው የህልውና ዘመቻ ላይ ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው በሁለተኛው የድጋፍ መርሀግብርም 85.7 ሚሊየን ብር ግምት ያለውን 609 በሬዎችን 1ሺህ 634 በጎችን እና ሌሎች የስንቅ ድጋፎች ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፡፡