በሀገር ደረጃ የፀረ ሙስና ትግል የሚያጠናክር ብሄራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተማችን አዲስ አበባም በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት 5 (አምስት) አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ ተሰይሟል፡፡
በዚህም መሰረት
1. ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ጀማል ረዲ የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙና ኮሚሽን ኮሚሽነር
3. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ
4. አቶ ጥላሁን ግድየለው የአዲስ አበባ ከተማ አቃቤ ህግ
5. ኮ/ር አህመድ መሃመድ የገቢዎች ቢሮ ም/ቢሮ/ሃላፊ ናቸው፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ በ 9977 የነፃ የስልክ መስመር አስፈላጊውን ጥቆማና መረጃ በመስጠት ለፀረ ሙስና ትግሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ከኮሚቴው ጎን እንዲቆም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
እንደ ሃገርም ይሁን እንደ ከተማ የተጀመረነውን የፀረ ሙስና ንቅናቄ ለመግታትና ለማሰናከል በማሰብ ፤ የተለያዩ ደባል አጀንዳዎችን በመፍጠርና በተለይ ትምህርት ቤትን የሁከት ማእከል ለማድረግ በከተማችን የተደራጀ ቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን ህዝቡ አውቆ በንቃት በመከታተል ይህንን ሴራ እንዲያከሽፍና የፀረ ሌብነት ትግሉ የማይቋረጥ መሆኑን በመገንዘብ ለኮሚቴው አስፈላጊውን ማስረጃና ጥቆማ እንዲያቀርብና ትግሉን ከጫፍ እንዲያደርስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የከተማችንን ሰላም እናስጠብቃለን!!
ከሌብነት የፀዳች አዲስ አበባን በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ እናረጋግጣለን!!