በሰላም ጎዳና ስያሜ መርሀ ግብር ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፣ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፤ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራልና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባው መንገድን የከተማ አስተዳደሩ በክብርት ከንቲባዋ አማካኝነት የሰላም ጎደና ተብሎ ተሰይሟል።
በሰላም ጎዳና ስያሜ መረሀ ግብር ላይ ከንቲባ አዳነች እንደተናገሩት በቅርብም በሩቅም ለወዳጆችችንም ሆነ ለሌሎች የምናስተላልፈው መልዕክት ዋናው ዛሬ መንገድ የመሰየማችን ዓላማ አጠቃላይ <<የኢትዮጵያ ጉዞ የሰላም መሆኑን ለተቀረው ዓለም ማመላከት ነው>> ብለዋል ።
ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ አስቀድማ ለሰላም ዘርግታው የነበረው እጇ አለመታጠፉን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ለሚወጉን አካላት ሁሉ ለማሳወቅ እንወዳለን ብለዋል ከንቲባዋ
የኢፌደሪ የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ ብናልፍ አንዷለሞ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ለሰላም ለሰጡት የላቀ ስፍራና ለዚህ ጎዳና ሲያሜ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል
አክለውም እንደተናገሩት ለሰላም አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ከፍለን ሁላችንም በአንድነት የአገራችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚጠበቅብን በመሆኑ በሁሉም ረገድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል
ኢትዮጵያውያን የዕለት ተግባራቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ሰላም ቁልፍ በመሆኑ ለሰላም መረጋገጥ በየደረጃው አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ በነፍስ ወከፍ ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል ሚንስትሩ
በመንገድ ስያሜ መርሀግብር ላይ የተገኙ የተለያዩ የሐይማኖት መሪዎች ኢትዮጵያ ወጣቶች ሰርተው የሚለወጡባትና አረጋዊያን የሚጦሩበት አገር እንድትሆን ከሁሉም በላቀ የኃይማኖቶች ለአገር ብልጽግና መጸለይን
፣የሕዝብ ለሕዝብ ወንድማማችነትና ትስስር እንዲጎለብት መስራትን ጨምሮ በላቀ ግብረገብነት ወጣቶች የዕድሜ ታላላቆቻቸውን የሚያከብሩ ፣በአንድነት የሚያምኑና አገራቸውን የሚወዱ እንዲሆኑ ኃይማኖቶች ማስተማርና መምከር እንዳለባቸው አሳስበዋል ።