በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የገንዘብ ድጋፍ በኩል የተመቻቸው የመንገድ ጥገና ማሽነሪዎች ግዢ ስምምነት የአ/አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አንጂነር ሞገስ ጥበቡ ከጃፓኑ ፊቸርበድ አለምእቀፍ ሊሚትድ ድርጅት ተወካይ አያሚ ናካዎ ጋር በበየነ መረብ ተፈራርመዋል ።
በፈርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር የደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትጵያና ጃፓን ግንኙነት ከ90 ዓመት በላይ የቆየና ወሳኝ በሆኑ በትምህርት፥ በቴክኖሎጂ የሚያደርጉትን ድጋፍ አድንቀዋል ::
ዛሬም ያልተቋረጠ ድጋፍቸው በከተማችን በትራንስፖርት ዘርፉ ወሳኝ በሆነው መንገድ ጥገና በሚጠቅም መሳሪያ ግዥ ደግፈውናል ብለዋል።
ድጋፍ በአ/አበባ የተሻለ የመንገድ አገልግሎት በሚገባ መስጠት እንድንችል ያግዘናል ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢ ድርጅቱ በወቅቱ እንደሚያቀርብም እምነታቸውን ገልፀዋል።
መንገድ አገልግሎቶችን ከሰው ጋር ለማገናኘት ወሣኝ መሠረተ ልማት ነው ያሉት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ታካኪ ኦቶ የዲፕሎማቲክ ማዕከል የሆነችው አ/አበባ መንገዶቿ ወብ እና ያማሩ እንዲሆኑ ዛሬ የተፈረመው የማሽነሪ ግዢ ድጋፍ አስተዋፅዖ አለው ብለዋል።
ይህ ስምምነት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል እያከናወነ የሚገኘውን የመንገድ ሃብት ጥገና አቅም ይበልጥ በማጎልበት ውጤታማነቱን እንደሚያሳድግ ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ ተናግረዋል፡፡
ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ የመንገድ ጥገና ማሽነሪዎች ግዢ ስምምነት፣ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የመንገድ ጥገና አቅሙን በዓመት በ25 በመቶ እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡
በግዢ ውል ስምምነቱ መሰረት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን መስሪያቤት 81 ማሽነሪዎችን ከጃፓን መንግስት በግዢ ያገኛል፡፡
የማሸነሪዎች ግዢ የጨረታው ሂደት በሦስት ሎት ተከፍሎ የሚከናወን ሲሆን፣ በሎት 1 እና 2 የተዘረዘሩት የ81 ማሽነሪዎች ግዢ በዚህ ስምምነት መሰረት ይፈፀማል ተብሏል፡፡
ኢንጀነር ሞገስ ከተማዋ ካላት አዳጊ የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት በቀጣይም የመንገድ ሽፋኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከመንገድ መሰረተ-ልማቱ እድገት ጎን ለጎን በከተማዋ በየዓመቱ የሚኖረው ወቅታዊና ተከታታይ የመንገድ ጥገና ፍላጎት በዚያው ልክ እንደሚጨምርም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጲያ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ጋር ያላት ትብብር አዲስ አበባ መንገዶች እንደተቋም ሲዋቀር ጀምሮ እ/ኤ/አ በ1996 የተለያዩ የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ድጋፎች ከማድረግ የጀመረ ነው።
በትብብሩ እ/ኤ/አ ከ2015 እስከ 2018 ድረስ ደግሞ የመንገድ ጥገና አቅም ማሳደጊያ ፕሮጀክት ሲተገበር የቆየ ሲሆን ይህም የመንገድ ጥገናን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን ትልቅ አብርክቶ እንዳለው ተገልጿል።