በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው ውይይት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ ፣ የሴክተር ተቋማት፣ የሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
የከተማ አስተደደሩ ከፍተኛ አመራሮች በ2013 በጀት ዓመት የተገኙ ውጤቶችን እና የታዩ ጉድለቶች ይገመግማሉ ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ አመራሩ ግንዛቤ እንዲይዝና ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
የከተማች ነዋሪዎች በምርጫው የሰጠን ድምፅ በተሻለ ብቃትና በታማኝነት እንድንፈጽም አመራሩ አቅሙ ተገንብቶ፣ ጉድለቶቹን አርሞ የተሰጠውን ሥራ በብቃት መፈጸም አለበት ብለዋል ።
በ2014 በጀት ዓመትም በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን ተቋማዊ አሰራርን መሠረት ባደረገ መልኩ በማጠናከር እና በህብረተሰቡ በኩል የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ምክትል ከንቲባዋ ጠቁመዋል ።