ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ፣ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አካለ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በስራ መግቢያ ሰዓት ላይ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ትራንስፖርት አገልግሎት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ታክሲ ፣አሽከርካሪዎችን ፣ተራ አስከባሪዎች እና የትራስፖርት ተቆጣጣሪዎችን አነጋግረዋል።የከተማ አስተዳደሩም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ችግርን ለመቅረፍ ከአውቶቡስ አቅርቦት ጀምሮ የመሰረተ ልማት እና የትራፊክ ማኔጅመንት ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡